ስለ AppGallery እና ግላዊነት መግለጫ
AppGallery ሆንግ ኮንግ ውስጥ በተደራጀው የHuawei አካል በሆነው Huawei Services (ሆንግ ኮንግ) Co., Limited, (ከአሁን በኋላ "እኛ"፣ "በእኛ" ወይም "የእኛ" ተብሎ በሚጠራ) የሚቀርብ አገልግሎት ነው። ነጻ እና የሚከፈልባቸው መተግበሪያዎችን ማሰስ፣ መድረስ፣ ማውረድ እና ማስተዳደር የሚችሉበት የማከፋፈያ መድረክ ያቀርብልዎታል።
ይህ መግለጫ የሚከተሉትን ይገልጻል፦
1. ስለ እርስዎ የምንሰበስበው ውሂብ ምንድን ነው?
2. ውሂብዎን የምንጠቀመው እንዴት ነው?
3. ውሂብዎን የምናስቀምጠው ለምን ያህል ጊዜ ነው?
4. ውሂብዎን የምናጋራው እንዴት ነው?
5. የእርስዎ መብቶች እና አማራጮች ምንድን ናቸው?
6. እኛን እንዴት ነው ማግኘት የሚችሉት?
7. ይህን መግለጫ የምናድሰው እንዴት ነው?
1. ስለ እርስዎ የምንሰበስበው ውሂብ ምንድን ነው?
እንደ የ AppGallery አገልግሎት አካል የግል ውሂብዎን የምንሰበስበውና የምንጠቀመው በዚህ መግለጫ ውስጥ ለተጠቀሱት ዓላማዎች ብቻ ነው። የግል ውሂብ ማለት እኛ እርስዎን እንደ አንድ ተጠቃሚ ለይተን እንድናውቀዎት የሚያስችለን ማንኛውም መረጃ ማለት ነው።
የሚከተለውን ውሂብ ሰብስበን እናሰናዳለን፦
•የHUAWEI መታወቂያ የመለያ መረጃ፣ ለምሳሌ እንደ የመለያ ስም (ኢሜይል ወይም የስልክ ቁጥር)፣ መገለጫ ምስል፣ ቅጽል ስም፣ የትውልድ ቀን፣ የሀገር/ክልል ኮድ፣ የመለያ ለዪ እና የመለያ ለዪ አገልግሎት ቶከን።
•የመሳሪያ መረጃ፦ ለምሳሌ የመሳሪያ መለያ (በመሳሪያዎ የስርዓት ስሪት የሚወሰን ሆኖ እንደ SN፣ UDID ወይም IMEI ያሉ)፣ የቋንቋ ቅንብሮች፣ የመሳሪያ ሞዴል፣ የመሳሪያ ስርዓተ ክወና ስሪት እና የሮም ስሪት፣ የማያ ትልቀት እና ምስል ጥራት፣ የሞባይል ሀገር ኮድ፣ የማድረሻ ሀገር።
•የአውታረ መረብ መረጃ፦ ለምሳሌ እንደ የIP አድራሻ፣ የአውታረ መረብ አይነት፣ እና የአውታረ መረብ ግንኙነት ሁኔታ ያሉ።
•የአገልግሎት አጠቃቀም መረጃ፣ ለምሳሌ የAppGallery ስሪት ቁጥር እና የማውረጃ ምንጭ፣ መተግበሪያን በመጠቀም ቆይታ ጊዜ፣ የመተግበሪያ ንኪ እና ተጋላጭነት ጊዜያት፣ የመተግበሪያ ፍለጋ ታሪክ፣ መተግበሪያ የማውረድ እና የመጫን ታሪክ እና ውጤቶች፣ወደ መተግበሪያ በመለያ የመግባት ውጤቶች፣ የተራገፉ መተግበሪያዎች ዝርዝር፣ የመተግበሪያ ግዢ ትዕዛዝ መጠን፣ የታዘዘበት ጊዜ፣ የትዕዛዝ መታወቂያ፣ የተጫኑ መተግበሪያዎች ዝርዝር፣ የተጠቃሚ ሽልማት (ስጦታዎች) መዝገብ፣ የመተግበሪያ አስተያየቶች፣ የተጠቃሚ ስምምነት ምዝገባ መዝገብ፣ የመተግበሪያ ማስተዋወቂያ ሰርጥ መታወቂያ፣ ወደ መተግበሪያ ድህረ ገጽ መገናኛ፣ እና የምኞት ዝርዝር መተግበሪያዎች።
በHUAWEI AppGallery ማስተዋወቂያዎች ወቅት በአንዱ ላይ ሽልማት ካሸነፉ፣ የእርስዎ የማድረሻ አድራሻ እና የስልክ ቁጥር/ኢሜይል አድራሻ ሽልማቱን ለእርስዎ ለማድረስ ይሰናዳሉ።
በጎብኚ ሁነታ ላይ ሆነው HUAWEI AppGalleryን ከተጠቀሙ (በHuawei መታወቂያ መለያዎ ሳይገቡ) የሚከተለው ውሂብ ይሰበሰብና ይሰናዳል፦
•የመሳሪያ መረጃ፣ ለምሳሌ የመሳሪያ መለያ በመሳሪያዎ የስርዓት ስሪት የሚወሰን ሆኖ እንደ SN፣ UDID ወይም IMEI ያሉ፣ የቋንቋ ቅንብሮች፣ የመሳሪያ አይነት፣ የመሳሪያ ስርዓተ ክወና (EMUI) ስሪት እና የሮም ስሪት፣ የማያ ትልቀት እና የምስል ጥራት፣ የማድረሻ ሀገር።
•የአውታረ መረብ መረጃ፣ ለምሳሌ እንደ የIP አድራሻ፣ የሞባይል ሀገር ኮድ (MCC)፣ የሞባይል አውታረ መረብ ኮድ (MNC)፣ የአውታረ መረብ አይነት እና የአውታረ መረብ ግንኙነት ሁኔታ።
•የአገልግሎት አጠቃቀም መረጃ፣ ለምሳሌ እንደ የAppGallery ስሪት ቁጥር፣ መተግበሪያ የተከፈተበት እና የተዘጋበት ጊዜ፣ ንኪዎች፣ ተጋላጭነት፣ የመተግበሪያ ፍለጋ ታሪክ፣ መተግበሪያ የማውረድ እና የመጫን ታሪክ፣ መዝገቦች እና የስህተት መዝገቦች፣ የመተግበሪያ ማስተዋወቂያ ሰርጥ መታወቂያ፣ ወደ መተግበሪያ ድህረ ገጽ መገናኛ፣ እና የተጠቃሚ ስምምነት ምዝገባ መዝገብ።
አስፈላጊዎቹን አገልግሎቶችን ለእርስዎ ለማቅረብ AppGallery የመሳሪያዎን መረጃ ለማግኘት ስልክዎን መድረስ፣ እና የመጫኛ ፓኬጆችን ለማስተዳደር ማከማቻዎን መድረስ ያስፈልገዋል። እንዲሁም ፈቃዶችን በመሳሪያዎ ቅንብሮች ውስጥ ማስተዳደር ይችላሉ።
2. ውሂብዎን የምንጠቀመው እንዴት ነው?
የAppGallery አገልግሎቶችን ለእርስዎ ለማቅረብ እና የውል ግዴታዎችን ለሟሟላት፣ እርስዎ መተግበሪያዎችዎን ማሰስ፣ መድረስ፣ ማውረድ እና ማስተዳደር እንዲችሉ የግል ውሂብዎን መሰብሰብ ያስፈልገናል። ይህ እንዲሁም ማንነትን ለመለየት፣ አለመግባባትን ለመፍታት፣ ለደንበኛ ግንኙነት አስተዳደር፣ ለድጋፍ እና ግንኙነት፣ ለደንበኛ ቅሬታ አያያዝ፣ ጥገና፣ ለስርዓት ማዘመኛዎች፣ ለችግር ምርመራ እና ጥገና ውሂብዎን እንድናሰናዳ ያስችለናል።
በተጨማሪም፣ የግል ውሂብዎን በእርስዎ ፈቃድ ለሚከተሉት አላማዎች እንጠቀማለን፦
•ለትንተናዎች እና ለግንባታ አላማዎች፣ በተለያዩ የተጠቃሚ ቡድኖች የአጠቃቀም እንቅስቃሴ ላይ በመመስረት የተጠቃለሉ ቡድኖችን መፍጠርን ጨምሮ። ይህ እንዲሁም ተጠቃሚዎቻችን እንደ ደንበኞች ያላቸውን ፍላጎቶች እንድንረዳ እና የእኛን የአሁን እና የወደፊት አገልግሎቶች እና አቅርቦቶች ጥራት እና የተጠቃሚ ተሞክሮ እንድናሻሽል፣ እንዲሁም የዘመቻዎችን እና የማስተዋወቂያዎችን ውጤታማነት እንድንገመግም ያስችለናል። ከታች በ አንቀጽ 5.6 ላይ እንደተገለጸው እንደዚህ ያለውን የውሂብ መሰናዳት መቃወም ይችላሉ።
•ስለ እኛ ቅናሾች፣ የሽያጭ ማስተዋወቂያዎች እና ለገበያ ስራ ዓላማዎች ለመነጋገር እና እንዲሁም ለገበያ ስራ የተሰበሰቡ ዒላማ ቡድኖችን ለመፍጠር። የደንበኞችን ምርጫዎች ማወቅ አቅርቦታችንን እንድናነጣጥር እና የደንበኞቻችንን ፍላጎቶች እና ምኞቶች በተሻለ የሚያሟሉ ምርቶችን እና አገልግሎቶችን እንድናቀርብ ያስችለናል። ከታች በ አንቀጽ 5.6 ላይ እንደተገለጸው እንደዚህ ያለውን የውሂብ መሰናዳት መቃወም ይችላሉ።
•ምክሮችን በማቅረብ እና AppGallery ውስጥ የተነጣጠሩ መተግበሪያዎችን በማሳየት አገልግሎቶችን ግላዊነት የተላበሱ ለማድረግ የግል ውሂብዎን ልናሰናዳ እንችላለን። ከታች በ አንቀጽ 5.6 ላይ እንደተገለጸው እንደዚህ ያለውን የውሂብ መሰናዳት መቃወም ይችላሉ።
•ለመረጃ ደህንነት ዓላማዎች፥ ደህንነታቸው የተጠበቁ እና አስተማማኝ አገልግሎቶችን ለእርስዎ ለማቅረብ የተለያዩ ዓይነት አገልግሎቶችን ያለአግባብ መጠቀም እና ማታለሎችን አጣርቶ ለማግኘት ወይም ለመከላከል ጨምሮ።
•AppGallery ውስጥ የሚገኝ መተግበሪያ ላይ አስተያየት ከሰጡ፣ የመተግበሪያው አበልጻጊ በእርስዎ ግብረመልስ እና ደረጃ አሰጣጥ ላይ በመመስረት አገልግሎቱን እንዲያሻሽሉ ለመርዳት የእርስዎን አስተያየት እና ቅጽል ስም ይፋ እናደርግላቸዋለን።
በHUAWEI መታወቂያዎ ገብተው HUAWEI AppGalleryን ሲጠቀሙ፣ AppGallery መተግበሪያ ውስጥ ፈቃድዎን ከሰጡ በኋላ፣ ስለሚገኙ አዲስ መተግበሪያዎች፣ ክስተቶች እና ከስጦታ ጋር የተገናኙ እንቅስቃሴዎች እርስዎን ለማሳወቅ ተገፊ ማሳወቂያዎችን ወደ መሳሪያዎ ልንልክ እንችላለን። ወደ AppGallery > እኔ > ቅንብሮች በመሄድና ማሳወቂያዎችን ስራ በማስቆም ፈቃድዎን በማንኛውም ጊዜ መሻር ይችላሉ።
እንዲሁም የእርስዎን የመተግበሪያ ግዢ ትዕዛዝ መጠን፣ የታዘዘበት ጊዜ እና የትዕዛዝ መታወቂያን እኛን በሚመለከቱ ህጎች እና ደንቦች እንደተፈለገው ለግብር እና ለሒሳብ ስራ ዓላማዎች ልናሰናዳ እንችላለን።
3. ውሂብዎን የምናስቀምጠው ለምን ያህል ጊዜ ነው?
የግል ውሂብዎን የምናስቀምጠው በዚህ መግለጫ ውስጥ ለተጠቀሱት ዓላማዎች አስፈላጊ እስከሆነበት ጊዜ ድረስ ብቻ ነው።
የእርስዎን ውሂብ ከእኛ ጋር ባለዎት የደንበኛ ግንኙነት ቆይታ ጊዜ ውስጥ እናሰናዳለን እና እናስቀምጣለን። የHUAWEI መታወቂያዎን መለያ ከሰረዙ፣ ከመለያዎ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሁሉም የግል ውሂብ እና አገልግሎቶች፣ AppGallery መተግበሪያን ጨምሮ፣ ይደመሰሳሉ። ይሁንና፣ የሚከተሉትን ለተገለጹት ጊዜያት እናቆያለን፦
•የመተግበሪያ ግዢ ትዕዛዝ መጠንን፣ የታዘዘበት ጊዜን እና የትዕዛዝ መታወቂያን ክፍያው ከተፈጸመ ጀምሮ ለሰባት (7) ዓመታት።
•ለደንበኛ ግንኙነት አስተዳደር የተሰናዳ የግል ውሂብ፣ ለምሳሌ የውሂብ ጉዳይ ጥያቄዎች፣ ቅሬታዎች፣ እና የደንበኛ መስተጋብር መዝገቦችን ከመጨረሻው መስተጋብር አንስቶ ለስድስት (6) አመታት።
•ለውል አስተዳደር ዓላማዎች የተሰናዳ የግል ውሂብን የHUAWEI መታወቂያዎ ከተሰረዘ በኋላ እስከ ሶስት (3) ዓመታት ድረስ።
•ለስታቲስቲካዊ ትንተና እና ለምርት ግንባታ፣ እንዲሁም ለሽያጭ ማስተዋወቂያ እና ለገበያ ማስፋፋት ዓላማዎች የተሰናዳ የግል ውሂብን ከተሰበሰበበት ቀን አንስቶ እስከ አስራ ሁለት (12) ወራት፣ እንደዚህ ያለ ማሰናዳትን ከተቃወሙ በስተቀር።
•የእርስዎን አድራሻ እና የስልክ ቁጥር/ኢሜይል አድራሻ፣ ሽልማቱ ለእርስዎ ከተላከ በኋላ ለአንድ (1) አመት።
•የእርስዎን ውሂብ እና አገልግሎቶች ደህንነት ለማረጋገጥ የሚሰናዱ የውሂብ ምትኬዎች እና የመተግበሪያ መዝገቦች፣ ከተፈጠሩበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስት (6) ወራት።
•አገልግሎቱን በጎብኚ ሁነታ ሆነው በሚጠቀሙበት ጊዜ የእርስዎ የአውታረ መረብ መረጃ እና የአጠቃቀም መረጃ ለ 7 ቀናት ይሰናዳል።
አንዴ የማቆያ ጊዜው ካበቃ በኋላ በሚመለካታቸው ህጎችና ደንቦች ከተጠየቀ በስተቀር የእርስዎን የግል ውሂብ እንሰርዘዋለን ወይም ማንነት እንዳይገልጽ እናደርጋለን።
4. ውሂብዎን የምናጋራው እንዴት ነው?
የእርስዎን ውሂብ የምናከማቸው ሲንጋፖር እና ሆንግ ኮንግ ውስጥ ባሉ የውሂብ ማዕከሎች ውስጥ ነው።
የእኛ የጥገና ክወናዎች ውሂብዎን ከህንድ እና ከቻይና እንድንደርስበት ሊያስፈልጋቸው ይችላል። በተጨማሪም፣ በሚኖሩበት አካባቢ የሚወሰን ሆኖ የእርስዎ ውሂብ በሌሎች ሀገሮች ለምሳሌ፣ በሜክሲኮ፣ ግብጽ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሳኡዲ አረቢያ፣ ፓኪስታን፣ ሚያንማር፣ ህንድ እና ማሌዥያ በሚገኙ አካባቢያዊ የደንበኛ አያያዝ ማዕከሎቻችን ውስጥ ሊሰናዳ ይችላል።
የእርስዎን ውሂብ የምናጋራው፦
•AppGallery ውስጥ የሚገኝ መተግበሪያ ላይ አስተያየት ሲሰጡ፣ የእርስዎ አስተያየት፣ ቅጽል ስም፣ የመሳሪያ ሞዴል እና አስተያያት የተሰጠበት ጊዜ አገልግሎትን ለማሻሻል እና/ወይም ችግሮችን ለማስተካከል ለመተግበሪያው አበልጻጊ ይፋ ይደረጋሉ።
•በሚመለከታቸው ህጎች መሠረት ወይም ከህጋዊ ሂደት ጋር በተያያዘ ለህጋዊ ሂደት ወይም ህጋዊ ስልጣን ካለው አካል ለመጣ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ሲያስፈልግ።
•እንደ ውህደት፣ የውርስ፣ የንብረቶች ሽያጭ (እንደ የአገልግሎት ስምምነቶች ያሉ) ወይም እንደ የአገልግሎት ወደ የHuawei ቡድን አካል ወይም ወደ ሌላ ኩባንያ የመሸጋገር አካል ሆኖ ሲያስፈልግ።
5. የእርስዎ መብቶች እና አማራጮች ምንድን ናቸው?
የሚከተሉት መብቶች እና አማራጮች አሉዎት፦
5.1 ውሂብዎን መድረስ
መሳሪያዎ ላይ ወደ ቅንብሮች > HUAWEI መታወቂያ > የግላዊነት ማዕከል > ውሂብዎን ይጠይቁ በመሄድ ከAppGallery ጋር በተያያዘ ሰብስበን ያስቀመጥነው የግል ውሂብዎን ቅጂ እና ገለጻ መጠየቅ ይችላሉ።
ለተጨማሪ የመዳረሻ ጥያቄ፣ በጎብኚ ሁነታ ውስጥ ሆነው AppGalleryን ሲጠቀሙ የውሂብዎን ቅጂ መጠየቅን ጨምሮ፣ እባክዎ ያነጋግሩን (https://consumer.huawei.com/ uk/legal/privacy-questions/)።
5.2 ውሂብዎን ማስተካከል
ውሂብዎ ወቅቱን የጠበቀ እና ትክክለኛ እንደሆነ ለማቆየት፣ ወደ ቅንብሮች > HUAWEI መታወቂያ በመሄድ ውሂብዎን መድረስ እና ማስተካከል ይችላሉ።
ወደ AppGallery > እኔ > ቅንብሮች > የመላኪያ መረጃ በመሄድ የእርስዎን የመላኪያ መረጃ መድረስ እና ማስተካከል ይችላሉ።
5.3 ውሂብዎን ማዛወር
መሳሪያዎ ላይ ወደ ቅንብሮች > HUAWEI መታወቂያ > የግላዊነት ማዕከል > ውሂብዎን ይጠይቁ በመሄድ ከAppGallery ጋር በተያያዘ ለእኛ ያቀረቡትን የግል ውሂብ በተለምዶ ስራ ላይ በሚውል እና በማሽን ሊነበብ ወደሚችል ቅርጸት ማዛወር ይችላሉ።
እንዲሁም አገልግሎቱን በጎብኚ ሁነታ ላይ ሆነው በሚጠቀሙበት ጊዜ AppGallery ውስጥ ለእኛ የሰጡትን የግል ውሂብ እኛን በማነጋገር በተለምዶ ስራ ላይ በሚውል እና በማሽን ሊነበብ ወደሚችል ቅርጸት ማዛወር ይችላሉ።
5.4 ውሂብዎን መደምሰስ
እርስዎ በማንኛውም ጊዜ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፦
•ወደ AppGallery > እኔ > የግዢ ታሪክ በመሄድ የእርስዎን የመተግበሪያ ማውረድ እና መጫን ታሪክ እና የግዢ መዝገቦች መሰረዝ።
•ወደ AppGallery > እኔ > ስጦታዎች በመሄድ የእርስዎን የስጦታዎች መዝገቦች መሰረዝ።
•ወደ AppGallery > እኔ > የምኞት ዝርዝር በመሄድ የምኞት ዝርዝር ውስጥ ያሉ መተግበሪያዎችን መሰረዝ።
•ወደ AppGallery > እኔ > ቅንብሮች > የመላኪያ መረጃ በመሄድ የእርስዎን የመላኪያ መረጃ መሰረዝ።
•የHUAWEI መታወቂያ መለያዎን መሰረዝ። በዚህም ምክንያት፣ ከHUAWEI መታወቂያዎ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሁሉም የግል ውሂብ እና አገልግሎቶች ይደመሰሳሉ፣ AppGallery ውስጥ ያለ የግል ውሂብዎን ጨምሮ።
•በአንቀጽ 5.6 ውስጥ በተገለጸው መሠረት የውሂብዎን መሰናዳት መቃወም። ተቃውሞዎ ትክክለኛ ከሆነ እና ውሂብዎን ማሰናዳቱን ለመቀጠል ሕጋዊ መሰረት የሌለን ከሆነ በእርስዎ ሕጋዊ ተቃውሞ ወሰን ውስጥ የሚወድቀውን ውሂብ እንደመስሳለን።
•የግል ውሂብዎ መሰናዳት ህገወጥ እንደሆነ እና ውሂብዎ መደምሰስ እንዳለበት ካሰቡ ያነጋግሩን (https://consumer.huawei.com/ uk/legal/privacy-questions/)።
የግል ውሂብዎን ቀድመው ባሳዩት ድርጊቶችዎ ላይ በመመስረት እና አንቀጽ 3 ውስጥ በተገለጹት የማቆያ ጊዜዎች ላይ በመመስረት ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ ውስጥ እንደመስሰዋለን ወይም ማንነት የማያሳውቅ እናደርገዋለን።
5.5 የሰጡትን ፈቃድ መሻር
ከእኛ ኤሌክትሮኒካዊ ቀጥተኛ የገበያ ስራ ለመቀበል መርጠው ከነበር፣ ወደ AppGallery > እኔ > ቅንብሮች በመሄድና ማሳወቂያዎችን ተቀበልን ስራ በማስቆም የሰጡትን ፈቃድ መሻር ይችላሉ።
5.6 ማሰናዳትን መቃወም
የእርስዎ ውሂብ ለትንተናዎች፣ ለምክሮች፣ ለግንባታ ወይም ለሽያጭ እና ለገበያ ስራ አላማዎች መሰናዳታቸውን መቃወም ከፈለጉ፣ እባክዎን ያነጋግሩን (https://consumer.huawei.com/ uk/legal/privacy-questions/)።
ጥያቄውን ሲያቀርቡ እባክዎ የጥያቄውን ወሰን ይግለጹ እና አገልግሎቱን በመለያ ገብተው የተጠቀሙ ከሆነ፣ ወደ HUAWEI መታወቂያዎ ለመግባት የተጠቀሙትን ኢሜይል አድራሻዎን ወይም የስልክ ቁጥርዎን ይስጡን፣ ወይም ደግሞ AppGalleryን በጎብኚ ሁነታ ሲጠቀሙ ከነበረ የመሳሪያ መለያዎን ይስጡን።
ባቀረቡት ጥያቄ ለመቀጠል የእርስዎን ማንነት ለማረጋገጥ እናነጋግርዎታለን።
5.7 ማሰናዳትን መገደብ
የግል ውሂብዎን መሰናዳት ለመገደብ ከፈለጉ እባክዎ ያነጋግሩን (https://consumer.huawei.com/ uk/legal/privacy-questions/)። እርስዎ በሚከተሉት ሁኔታዎች ስር የግል ውሂብዎን መሰናዳት የመገደብ መብት አለዎት፦
•ውሂብዎ ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ሲሰናዳ፣ ነገር ግን መደምሰስ ካልፈለጉ።
•ሊመሰርቱት፣ ሊጠቀሙት፣ ወይም ሊከላከሉት የሚያስፈልግዎት እና ውሂብዎን ሳንጠብቅ ስንቀር እንድንጠብቀው ሊጠይቁን የሚችሉት ህጋዊ የይገባኛል ጥያቄ ሲኖርዎት።
•የግል ውሂብዎን ትክክለኛነት ተጠራጥረው ተቃውሞ ሲያስገቡ እናም የውሂብዎ ትክክለኛነት በእኛ መረጋገጥን በመጠባበቅ ላይ ሲሆን።
•የተቃውሞ ጥያቄዎ በእኛ መረጋገጥን በመጠባበቅ ላይ ሲሆን።
ባቀረቡት ጥያቄ ለመቀጠል የእርስዎን ማንነት ለማረጋገጥ እናነጋግርዎታለን።
6. እኛን እንዴት ነው ማግኘት የሚችሉት?
የውሂብ ጉዳይ መብቶችዎን እንዴት እንደሚጠቀሙ ለማወቅ አንቀጽ 5 ውስጥ መመሪያ ማግኘት ይችላሉ። እንደ የውሂብ ጉዳይ የእርስዎ መብቶች ላይ ወይም የግል ውሂብዎ በእኛ መሰናዳቱ ላይ ማንኛውም ጥያቄዎች፣ አስተያየቶች፣ ወይም ምክረ ሀሳቦች ያለዎት ከሆነ ወይም ደግሞ የእኛን የውሂብ ጥበቃ ኃላፊ ማነጋገር ከፈለጉ፣ እባክዎን ያነጋግሩን (https://consumer.huawei.com/ uk/legal/privacy-questions/)።
የዋና መስሪያ ቤታችን አድራሻ፦ Huawei Services (ሆንግ ኮንግ) Co., Limited, ክፍል 03፣ 9ኛ ፎቅ፣ ታወር 6፣ ዘ ጌትዌይ፣ ቁ.9 ካንቶን መንገድ፣ ጺም ሻ ጹ፣ ኮውሉን፣ ሆንግ ኮንግ። የምዝገባ ቁጥር 1451551።
እኛ የእርስዎን የግል ውሂብ በዚህ መግለጫ ወይም በሚመለከታቸው የውሂብ ጥበቃ ሕጎች መሰረት አናሰናዳም ብለው ካመኑ፣ የእርስዎ የውሂብ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር ወይም ሆንግ ኮንግ ውስጥ ያለ የግል ውሂብ ጥበቃ ኮሚሽነር ጋር ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ።
7. ይህን መግለጫ የምናድሰው እንዴት ነው?
ይህን መግለጫ በመጪዎቹ ጊዜያት ልናድሰው ስለምንችል በመተግበሪያ ቅንብሮች ውስጥ በየጊዜው የቅርብ ስሪቱን እንዲያጣሩ እናበረታታዎታለን። በዚህ መግለጫ ላይ ጉልህ ለውጦች በሚደረጉበት ጊዜ፣ በለውጡ ተፈጥሮ የሚወሰን ሆኖ በማሳወቂያ የንንግር ሳጥኖች፣ በተገፊ መልዕክቶች፣ በኢሜይሎች እና በመሳሰሉት መንገዶች አስቀድመን እናሳውቅዎታለን።
መጨረሻ የታደሰው፦ ሴፕቴምበር 2019